Saturday, January 24, 2015

በሰሜን ጎንደር ዞን የሚኖር ህዝብ የምርጫ ካርድ እንዲይዝ በስርአቱ ካድሬዎች የወረደውን ትእዛዝ እየተቃወመው መሆኑን ተገለፀ።



በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ላይ እና ታች አርማጭሆ የሚገኝ ወገናችን የምርጫ ካርድ ለመያዝ መመዝገብ እንዳለበት በብአዴን ኢህአደግ አስተዳደርና ካድሬዎች የቀረበለትን ተደጋጋሚ ቅስቀሳ ለማን እንድንመርጥ ነው የምርጫ ካርድ የምንይዘው በማለት እንዲካሄድ ታስቦ ያለውን የስርአቱ አስመሳይ ምርጫ እንዳልተቀበሉት ምንጮቻችን ከአካባቢው ከላኩልን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው በስልጣን ላይ ያለው ስርአት ልክ እንደሌሎች የሃገራችን አካባቢዎች እያካሄደው እንዳለው በዚህ ዞንም ካለፈው ጥር 1/ 2007 ዓ/ም ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ በሚል የምርጫ ጣቢያዎችን ከፍቶ ህዝቡ የምርጫ ካርድ እንዲይዝ ቅስቀሳ አድርጎ ሊሆንለት ባለመቻሉ ምክንያት በዚህ ፈንታ በትእዛዝ ወደ ምርጫ ጣብያው እንዲሄዱ ለማድረግ  ቢሞክርም እስከ አሁን ድረስ ግን ህዝቡ ቃሉን በመጠበቁ ምክንያት የስርአቱ ባለስልጣናት በከባድ ጭንቀት ላይ ተውጠው እንደሚገኙ ታወቀ።