Thursday, January 22, 2015

በሁሉም የትግራይ ዞኖች ውስጥ ዕድሜ በማይለይ ሁኔታ ለሚሊሻዎች እየተሰጠ ያለው ወታደራዊ ስልጠና በተለይ በእድሜ የገፉ አዛውንቶች በፊት ያገለገልነው ይበቃናል መሳርያችሁን ተቀበሉን እንዳሏቸው ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የደረሰን መረጃ ገለጸ።



    በትግራይ ክልል የሚገኙ ሚሊሻዎች እድሜን በማይለይ ሁኔታ በህወሃት ካድሬዎች ቀጥታዊ አመራር በተከታታይ ወታደራዊ ስልጠና ላይ መጠመዳቸውን የገለጸው መረጃው በተለይ በእድሜ የገፉት አዛውንቶች ከዚህ በፊት ያገለገልነው ይበቃናል፤ መሳርያችሁን ተቀብላችሁ አሰናብቱን በማለት ወደ ሚመለከታቸው የስርአቱ ባለስልጣናት ብሶታቸውን ቢያቀርቡም የተሰጣቸው መልስ ቢኖር አገሪትዋን ማን ሊጠብቃት ትፈልጋላችሁ አናሰናብታችሁም በማለት ጥያቄያቸውን ውድቅ እንዳደረጉት የተገኘው መረጃ አስታውቋል።
    ስልጣን ላይ ያለው አምባገነኑ የኢህአዴግ ስርአት ከህዝቡ ተነጥሎ ስለሚገኝ ካለበት ስጋት ተነስቶ ህዝቡን በመሳርያ ሃይል ለማምበርከክ በማሰብ ታጣቂዎችን በወተሃደራዊ ስልጠና ላይ ጠምዷቸው እንደሚገኝ በተደጋጋሚ መግለፃችን ይታወቃል።