በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የሚገኙ የስርዓቱ
ካድሬዎች የመድረክ አባላት የሆኑ ንፁሃን ዜጎቻችንን እየጠለፉ በማጥፋት ላይ እንደሆኑ የገለፀው ይህ መረጃ ከተጠለፉት መካከል የተወሰኑትን
ለመጥቀስ፤ አቶ ቴዎድሮስ መለስ፤ ወ/ሮ ሪዒማ ከድር፤ በባህር ዳር ዩንቨርስቲ መምህር የነበረው አቶ ተፈራ ማሙና ሌሎችንም የመድረክ
አባላት ታህሳስ 27/2007 ዓ,ም ተጠልፈው ከተወሰዱበት ዕለት እስካሁን የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ለማወቅ ተችሏል።
የኢህአዴግ ባለስልጣናት በግንቦት ወር 2007 ዓ.ም አካሄደው አለሁ ለሚልለት
አስመሳይ ምርጫ ለተቃዋሚ ድርጅቶች በህዝብ ዘንድ ሊመረጡ ይችላሉ ላላቸው ዜጎች ማስረጃ የሌለው የሓሰት ወንጀል እየፈጠረ በማሰር
ላይ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።