በትግራይ ክልል በመቐለ፤ ዓዲ-ግራት፤ ውቕሮ
ክልተ አውላዕሎ፤ ዓድዋ፤ እንትጮና ሌሎች ከተሞች ቤት የሌላቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች መኖርያ ቤት እንዲሰሩ ተብሎ ለእደላ የተዘጋጀውን
መሬት በጉቦና በአድልዎ እየተከፋፈለ መሆኑን የገለፀው መረጃው በተለይ የማዘጋጃ ቤቶችና የወረዳዎቹ አስተዳዳሪዎች ታህሳስ
24/2007 ዓ/ም ለሃብታሞች ብቻ ሲያድሏቸው የታዘቡ የከተማዎቹ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን በተቃውሞ መልክ መግለፃቸውን የተገኘው መረጃ
አስታውቋል።
የስርአቱ ካድሬዎች በህዝቡ እየተነሳ ያለው ተቃውሞ ስጋት ስለሆነባቸው
የመሬት እደላውን እንዳቆሙት የገለፀው መረጃው የተቋረጠው የመሬት እደላ ሲጀመር ተቃውሞ ለማንሳት በሚሞክር ላይ ግን አስፈላጊውን
እርምጃ ይወሰድበታል በማለት ህዝቡን እያስፈራሩት እንደሚገኙ ከተለያዩ የትግራይ ከተሞች ያገኘነው መረጃ አስረድቷል።