Thursday, January 22, 2015

በአማራና በትግራይ ክልል መካከል መነሻውን መሬት ያደረገው ግጭት በኦሮሚያ ክልል አስተዳዳሪ የተደረገው የማስታረቅ ሂደት ለህብረተሰቡ ማዕከል ያደረገ ባለመሆኑ የሚያመጣው ለውጥ እንደማይኖር ተገለፀ።



በሁለቱ ክልሎች መካከል ተፈጠሮ ያለውን ግጭት እንዲፈታ በማለት ለማስመሰል በኦሮሚያ ክልል አስተዳዳሪ ጥር 2እና 3/2007 ዓ.ም ለማስታረቅ ተሞክሮ እንደነበረ የገለፀው መረጃው በእርቁ ላይ ከተገኙት የክልል አንድ አስተዳተዳዳሪዎች ውስጥ የትግራይ ክልል ፕሬዝደት አባይ ወልዱ፤ የክልሉፖሊስ ኮሚሽነር ዘአማኔል ለገሰ/ወዲ ሻምበል/ የፀጥታ ሓላፊው ሓዲሽ ዘነበ፤ ሲሆኑ ከክልል ሶስት ደግሞ የክልሉ ፕሬዝደት የፀጥታ ሓላፊውና ኮሚሽነሩ እንደሆኑ ታውቋል።
   ተደርጓል የተባለው እርቅ ለከፍተኛ አስተዳዳሪዎች ብቻ ካልሆነ በስተቀር ለነዋሪው ህዝብ ማዕከል ያደረገ ባለመሆኑ አወንታዊ ውጤት እንደማይኖረው የገለፀው መረጃው በዚህ የተነሳም የክልል ሶስት ሓላፊዎች ግጭቱ ወደ ተከሰተበት አካባቢ ለመሄድ ሃይለኛ ስጋት ስላደረባቸው ከጎንደር ከተማ በብዙ ታጣቂዎች ተጅበው መሄዳቸው በአካባቢው ህዝብ ያላቸው ተቀባይነት ዝቅተኛ መሆኑን የሚያመላክት ነው ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።