Sunday, January 25, 2015

በትግራይ ማእከላዊ ዞን አህፈሮም ወረዳ ውስጥ የሚኖረው ህዝብ በህወሃት ካድሬዎች ተገዶ የምርጫ ካርድ እየወሰደ መሆኑን ምንጮቻችን ከአካባቢው ገለፁ።



በተገኘው መረጃ መሰረት ስርአቱ በመላው ያገራችን ክፍል የምርጫ ካርድ ማደል በጀመረበት ግዜ በአህፈሮም ወረዳም በተመሳሳይ ካርዱ እየተሰጠ መሆኑን የገለጸው መረጃው አንድ ወላጅ ለሁሉም ቤተሰብ የሚሆን የምርጫ ካርድ በሃላፊነት መውሰድ ካልቻለ በአካባቢው አስተዳዳሪዎች የተለያዩ ጫናዎች እንደሚደርሰበት ታውቋል።
    ከእድሜ በታች የሆነው ዜጋ ያላመነበትን ምርጫ በወላጆቹ እጅ ተጠቅመው የምርጫ ካርድ እንዲሰጥ ማድረግ ህገ መንግስት ላይ የሰፈረውንና ምርጫን አስመልክቶ የተፃፈውን አንቀፅ የሚጥስ እንደሆነና ይህ ድርጊትም የኢህአዴግ ቡድን በስልጣን ላይ እንዲቀጥሉ ለማድረግ እየተከተሉት ያለውን የማደናገር ተግባር አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑን መረጃው አክሎ አስረዷል።