Sunday, January 25, 2015

በትግራይ ክልል የሚገኙ ወጣቶች የምርጫ ካርድ ተገደው እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑን ተገለጸ።



ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው ህዝቡ መጪው ግንቦት ወር 2007 ዓ/ም እንዲደረግ ታስቦ ያለውን የስርዓቱ አስመሳይ ምርጫ ስላላመነበትና በተለይ ወጣቱ ሃይል የምርጫ ካርድ አንወስድም በማለቱ ምክንያት በህወሃት ካድሬዎች “ሰላዮች” የሚል ስም ተሰጥቷቸው እየተሰደቡና የማስፈራራት ዛቻ እየደረሰባቸው መሆኑን ታወቀ።
   እንደወጣቶቹ አገላለፅ! የምርጫ ካርድ አንወስድም አንመርጥም ማለታችን መብታችን ነው፤ የስልጣን ዕድሜያችሁን ለማራዘም በማሰብ ህዝቡ የሚደግፋቸው የተቃዋሚ ድርጅት አባላትን እንዲታሰሩ ስላደረጋችሁ ማንንም አንመርጥም አታስገድዱን በማለት ተቃውሟቸውን እያሰሙ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረዷል።