Sunday, January 25, 2015

ማህበራዊ ችግር ላጋጠማቸው የአህፈሮም ወረዳ ነዋሪዎች ተብሎ ከእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች የተገኘው እህል ለህ.ወ.ሃ.ት ገንዘብ እየከፈሉ እንዲወስዱ መገደዳቸው ተገለፀ።



     ከአካባቢው የደረሰን መረጃ እንዳስታወቀው በትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ በአህፈሮም ወረዳ የሚገኙ የህ.ወ.ሃ.ት አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች ከለጋሽ አገሮች የህብረተሰቡን ማህበራዊ ችግሮችን ለማቃለል ተብሎ የተላከውን የምግብ እርዳታ ስርዓቱ በቀጥታ ለተጠቃሚው መስጠት ሲገባው ለፖለቲካ መጠቀሚያ እያዋለው መሆኑን የገለጸው መረጃው፣ ማንኛውም ግለሰብ የእርዳታ እህል ለመውሰድ ከፈለገ በመጀመርያ የድርጅቱ አባል ለመሆን እንደሚገደድና እርዳታው ሲሰጠውም በወረዳው አስተዳዳሪዎች ገንዘብ ለመክፈል እንደሚገደድ ተገልጿል።
    ይህ ከያንዳዱ እርዳታ ተቀባይ ግለሰብ ያለ አንዳች ህጋዊ ደረሰኝ ለህወሃት አባልነት፤ ለትግራይ ልማት ማህበር፤ ለማህበራዊ ጉዳይ፤ ለእንግዶች መቀበያ በሚል በአስገዳጅነት ከህዝቡ የሚሰበሰበው በመቶ ሺዎች የሚገመት ገንዘብ ለግል ጥቅማቸውና ለድርጅቱ ማጠናከርያ እያዋሉት መሆናቸውን ምንጮቻችን ከቦታው አስታውቋል።