Saturday, January 24, 2015

በትግራይ ክልል የሚገኙ ወጣት ተማሪዎች ወደ ውትድርና እንዲገቡ በህወሓት-ኢህአደግ ካድሬዎች በአስገዳጅ ስብሰባ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ተገለጸ።



    በካሃዲው የኢህአደግ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ የትግራይ ተወላጆች ቁጥር አንሷል በማለት የህወሓት ኢህአደግ ካድሬዎች ወደ ትምህርት ቤቶችና ሌሎች የስራ ዘርፎች በመሄድ የትግራይ ወጣት ተማሪዎች ወደ ውትድርና እንዲገቡ የአስገዳጅ ሰብሰባ እያካሄዱባቸው መሆኑን ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ አስረድቷል።
    እንደ መረጃው አገላለፅ በትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን ላዕላይ ማይጨው ወረዳ አስተዳደሪ  ፍስሃ በዛብህ የተባለ የአካባቢውን ህብረተሰብ  ተማሪዎችንና ወጣቶችን ሰብሰቦ በመከላከያ አጋጥሞ ያለውን የትግራይ ተወላጆች ቁጥር ማነስ የግድ መሸፈን አለብን፤ ወጣቱም እንድሄድ ንገሩት፤ ከዚህ ያለፈ ግን በግዴታ እንደምንወስደው ማወቅ አለበት በማለት ማስፈራራት የተሞላበት ስብሰባ እንዳካሄደባቸው ለማወቅ ተችሏል።