Monday, February 23, 2015

የሁመራ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የኢህአዴግን ፀረ ህዝብ አካሄድ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ከከተማዋ የደርሰን መረጃ አስታወቀ።



   በመረጃው መሰረት በትግራይ ምእራባዊ ዞን፤ የሁመራ 2 ደረጃ ተማሪዎች አስተማሪዎቹ የካቲት 11ን አስመልክተው ፖለቲካዊ ቅስቀሳ እያካሄዱ መደበኛ ትምህርት ማስተማር ባለመቻላቸው ተማሪዎቹ ይህን ሃላፊነት የጎደለው የስርዓቱ አካሄድ በመቃወም የካቲት 3/2007 ዓ/ም የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸው ተገለፀ።
    እነዚህ ቁጥራቸው ከ200 በላይ የሚሆኑ የ2 ደረጃ ተማሪዎች በተቃውሞው ሰልፍ ላይ እያሰሙት ከነበሩት መፈክሮች ለመጥቅስ ትምህርታችን እናቋርጥም፤ ከተለያዩ ቀበሌዎች የመጣን ተማሪዎች መንግስት በተገቢ መንገድ ሊያስተምረን አልቻለም፤ ለአንድ ፖለቲካዊ ፓርቲ ብቻ የሚደግፍ የትምህርት ፖሊሲ ያብቃ። የሚሉና ሌሎችም መሆናቸውን የገለጸው መረጃው የከተማዋ የፖሊስ አባላትም የምታካሂዱት ተቃውሞ ህጋዊነት የለውም በማለት አስፈራርተው እንደበተኗቸው ለማወቅ ተችሏል።