በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የህወሃት ከፍተኛ
ባለስልጣናት ዝቅተኛ ካድሬዎችን በመሰብሰብ የትግራይ ወጣቶች ለምን ኑሮውን እየጣለ ወደ ትጥቅ ትግልና ስደት ያመራል ሲሉ ላቀረቡላቸው
ጥያቄ የህዝባችን ፍላጎትና ጥያቄ ባለመመለሱ፤ በከባድ የኑሮ ችግር ላይ ወድቆ ስለሚገኝና በዚህ ዓይነት ኑሮ መኖር ስለመረረው ትጥቅ ትግል ወደ ሚያካሂዱ ድርጅቶችና ወደ ጎረቤት ሃገራት ስደት እንዲሄዱ
እየተገደዱ ናቸው በማለት እንደመለሱላቸው ለማወቅ ተችሏል።
እነኝህ ካድሬዎች በማስከተል የሄደ ሄዷል ያልሄደው ወጣትም ቢሆን ተቃውሞ
ለማካሄድ ጊዜና ቦታ እየጠበቀ ስለሆነ መንግስት መልካም አስተዳደርና ፍትህ በማንገስ ህዝቡን ሊያረጋጋ ይገባዋል ባሉበት ጊዜ እናንተ
ወጣቱ ክፍል እንዲሰደድ በማድረጉ እጃችሁ አለበት በማለት ከፍተኛ አመራሮች ማስፈራራት በመጀመራቸው ሳይረዳዱ መለያየታቸውን መረጃው
አክሎ አስረድቷል።