በወልቃይት ወረዳ የሚኖር ህዝብ የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ
መሪዎችን ጠልቷቸው ባለበት ጊዜ ጥር 29 ቀን 2007 ዓ/ም በወረዳ ደረጃ ስብሰባ የተካሄደ መሆኑን የገለፀው መረጃው መድረኩን
ይመራው የነበረው ሰለሙን እምባየ የተባለ የግብርናና ገጠር ልማት ፅህፈት ቤት ሃላፊ ከሌላ ጓደኛው ጋር በመሆን ከመንግስት ተበድራችሁ
የወሰዳችሁትን የማዳበሪያ ዋጋ እስከ ወለዱ ወደ ማረት ሳይውል ሳያድር ገቢ አድርጉ ይህንን ትእዛዝ የጣሰም ከደርግ ለይተን ስለማናየው
የደርግ እጣ ይደርሰዋል በማለት ነዋሪውን ህዝብ ሲያስፈራራው እንደዋለ ታውቋል።
ተሰብሳቢው ህዝብ በበኩሉ ደርግ የወደቀው ህዝባዊ ድጋፍ ባልተለየው የጀግኖች
ትግል እንጂ እንዲህ እንደናንተ ባሉ የግል ጥቅም በሚያሯሯጡ ስግብግቦች
አልተሸነፈም ተገድደን የወሰድነው ማዳበሪያም ፍሬ ሊሰጠን ስላልቻለ ገንዘብ የለንም የምታደርጉን ካለ ደግሞ በኋላ አብረን እናያለን
በማለት ህዝቡ በአንድነት ስብሰባውን አፍርሶ የተበተነ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።