Monday, February 23, 2015

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ዋልታ ኢፎርሜሽንና ፋና ቢሮ ውስጥ የሚገኙት ሰራተኞች አብዛኛዎቹ የስርአቱ አባላት መሆናቸውና በዘመድ አዝማድ የተቀጠሩ እንደሆኑ ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።



    በዋልታ ኢፎርሜሽን ማእከልና ፋና ፅ/ቤት ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞች ከግማሽ በላይ የስርዓቱ አባላትና በዘመድ አዝማድ የተቀጠሩ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው በተለይ የዋልታ ኢፎርሜሽን ማእከል ሃላፊ የሆነው አቶ ተተካ በቀለና የዋልታና ፋና ጥምረት የሆነው ዋፋ የተባለውን ጀኔራል ማርኬቲግ ድርጅት ሃላፊ የሆነችው ባለቤቱ ወይዘሮ ፋንታየ ጌታነህ 15 የሚያህሉ ሰራተኞች ዘመዶቻቸው ወደ ድርጅቱ እዲቀጠሩ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።
     በዚህ መሰረትም የፅ/ቤቱ ሰራተኞች ተከስቶ ባለው ቤተሰባዊ የአስተዳደር ሁኔታ እያማራሩ መሆናቸውን ምንጮቻችን አክለው አስረድቷል።