ከተማው ውስጥ የሚገኙ ምንጮች አንደ ገለፁት
በትግራይ ደቡባዊ ዞን የኮሮም ከተማ ነዋሪ የሆነው የዋግነህ በለጠ የተባለው ካድሬ ጥር 21/2007 ዓ/ም ሌሊት ላይ ከኮረም ወደ
አላማጣ በሚወስዶው መንገድ ላይ በስለት ተወግቶ ህይወቱ አልፎ ማደሩን ተገለፀ።
የሞተው ምልሻ የስርዓቱ ዋናው ታማኝ እንደነበረና ህዝቡን እያሰቃየ መቆየቱን
የገለፀው መረጃው የአካባቢው ተወላጆች የበቀል እርምጃ እነደሚወስዱበት እየዛቱ መቆየታቸውና የመከላከያ ሰራዊት ሞቶ ባገኙበት ሰዓት
እስከሬኑን ለምርመራ መቐለ ድረስ መውሰዳቸውና በተጨማሪም የከተማው ፖሊስ ከሟቹ ጠብ ነበራቸው ያላቸውን ንፁሃን ወገኖች በጥርጣሬ
እያሰሯቸው መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።