በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን የሚገኘው የአክሱም
ዩኒቨርሲቲ በውስጡ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ለደህንነታቸው የሚደረግ ምንም ዓይነት ቁጥጥር አለመኖሩን የገለፀው መረጃው
በዚህ ምክንያትም ጥር 17 ቀን 2007 ዓ/ም ፍስሃ ዘውዴ የተባለ የአዲስ አበባ ተወላጅ የ5ኛ ዓመት ተማሪ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ
ተማሪዎች ለህይወታቸው ዋስትና ባለመኖሩ በፍርሃትና በጭንቀት ወድቀው እንደሚገኙ ታውቋል።
ሟቹ ዜጋ ከተገደለ በኋላ ገዳዩን ለማወቅ የሚመለከታቸው
አካላት የነቃ የማጣራት እንቅስቃሴ ባለማድረጋቸው በዩኒቨርሲቲው መፍትሄ ያጡ በርከት ያሉ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች በተማሪዎች
ሲካሄዱ ከቆዩ ተቃውሞዎች ጋር ተያይዞ በስርዓቱ በተሰማሩ የደህንነት አባላት ተግድሎ ሊሆን እንደሚችል የተማሪዎች ሙሉ እምነት መሆኑን
የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጨምረው አስረድተዋል።