ከከተማዋ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ምርጥ ገበያ ተብሎ በሚጠራው
የመንግስት ሸቀጦች ተሰማርተው እየሰሩ የሚገኙ 120 የሚደርሱ ወገኖቻችን
ደመወዛቸው ከሁለት ወር በላይ ሳይከፈላቸው በመቆየታቸው ምክንያት ጥር 29/2007 ዓ.ም ሸቀጣ ሸቀጥ አናራግፍም አንጭንም በማለት
ተቃውሞ እንዳካሄዱ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው እንደሚያስረዳው የተነሳው ተቃውሞ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዳይሸጋገር
የሰጉ የስርዓቱ ካድሬዎች ምን ያመጣሉ ከሚል የንቀት ባህሪያቸውና አስተሳሰባቸው የተንሳ ከልክለዋቸው የነበረውን ደመወዛቸውን በስቸኳይ
ለመክፈል እንደተገደዱ ታውቋል።