Friday, February 20, 2015

በህዝቡ ተቃውሞ የተደናገጡት የህወሃት ማሌሊት ባለስልጣናት ለሰማእታት ቤተሰቦች እናግዛለን እያሉ በማደናገር ተግባር ለይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ምንጮቻችን አስታወቁ።



በደረሰን መረጃ መሰረት ከፍተኛ የህወሃት አመራሮች ጥር 26/2007 ዓ.ም ጀምረው ለሰማዕታት ቤተሰቦች ልዩ ትኩረት ልናደርግላቸው ነው እያሉ በመቀስቀስ ላይ ቢሆኑም ምን አይነት እገዛ እንደሚያደርጉላቸው ሳይገልጹ እንዲሁ በደፈናው እየለፈለፉ መሆናቸውን የገለፀው ይህ መረጃ በዚህ የማደናገርያ ሃሳባቸው የተቆጣው ማህበረሰብ እንድትመረጡ ብላችሁ እያደረጋችሁት ያለ መላ ነው እንጂ ለሰማዕታት ቤተሰቦች ምንም አይነት ትኩረት እንደሌላችሁ ባለፉት 23 ዓመታት ታዝበናችኋል በማለት እየተቃዎሟቸው እንደሚገኙ መረጃው ገልጿል።
   የኢህአዴግ ቡድን ምርጫ በተቃረበበት ሰዓት ታማኝ ካድሬዎቹን በማሰማራት የማይተገበሩ ነገሮችን ለህዝቡ ቃል በመግባት የህብረተሰቡን አመለካከት ለማስቀየስ ሲል ሁልጊዜ  ላይ እና ታች ማለት የስርዓቱ መገለጫ ባህሪው መሆኑንና አሁንም ይህንን ተግባራቸውን በማጠናከር በሰማዕታት ስም እየማሉ የሰማታትን ቤተሰቦች ለማገዝ ተዘጋጅተናል ማለታቸው በዚህ አመት ይካሄዳል በተባለለት አስመሳይ ምርጫ ላይ አዲስ የቅስቀሳ ዜዴያቸው እየተጠቀሙ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።