Friday, February 20, 2015

በአዲስ አበባ ጦር ሃይሎች ሆስፒታል የሚገኙ በጦርነት የተጎዱ አካለ ስንኩላን በጎዳና ለወደቁ የአካል ጉዳተኛ ወታደሮች መንግስት አስፈላጊውን እርዳታ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቀረቡ።



በአዲስ አበባ የጦር ሃይሎች ሆስፒታል የሚገኙ በጦርነት የተጎዱ የአካል ጉዳተኞች ጥር 18 ቀን 2007 ዓ/ም ወደ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት ጠቅላይ ሚኒስተር ቢሮ በመሄድ “መንግስት ለምን በጦርነት የተጎዱትን የጎዳና ተዳዳሪ ወታደሮች አስፈላጊ እርዳታ አያደርግላቸውም የሚልና እኛ በሆስፒታል የምንገኝ ጉዳተኞችም እየተደረገ ባለው መጥፎ አያያዛችሁ ምክንያት ልንወጣ እየተገፋፋን ነን” በማለት የጠየቁ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው የስርአቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማሪያም ደሳለኝ በበኩሉም እኔ አካል ጉዳተኞችን በሚመለከት የማውቀው ጉዳይ የለኝም ብሎ ወደ ሳሞራ የኑስ የላካቸው መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አስረድቷል።
    ጀኔራል  ሳሞራ የኑስ በበኩሉ “ ይህ እያነሳችሁት ያለው ጥያቄ ረጂም ጊዜ ያስቆጠረና ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ አበላሽቶት ያለፈ በመሆኑ እኔ በዚህ ውስጥ እጄን አላስገባም” ሲል ጥያቄያቸውን በአግባቡ እንዳልመለሰላቸውና የሰጠው መልስም ለመሸሻና ማለፊያ የጠቀመበት መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።