Friday, February 13, 2015

በአዲስ አበባ የሚኖሩ የቀድሞ ወታደር ዜጎቻችን ብስርዓቱ ካድሬዎች የተደረገላቸውን ስብሰባ ረግጠውት እንደወጡ ምንጮቻችን ከአዲስ አበባ አስታወቁ።



የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው እነዚህ በአዲስ አበባ ከ1987 ዓ.ም ጀምረው ከመከላከያ ሰራዊት ተሰናብተው የቆዩ የኢህአዴግ ወታደሮች በጉለሌ  ክፍለ ከተማ በስርዓቱ ካድሬዎች ጥር 17/2007 ዓ.ም በተደረገላቸው ስብሰባ ላይ እናንተ አካላችሁን ሰንክላችሁ እዚህ ደረጃ ያደረሳችሁትን ስርዓት ለምን ትቃወሙት አላችሁ የሚል አስመሳይ አጀንዳ ባቀረቡላቸው ሰዓት የነበረውን ስብሰባ በመቃዎም ረግጠውት እንደወጡ ሊታወቅ ተችሏል።
   መረጃው አክሎ ስብሰባውን ይመራው የነበረው አበበ የተባለ ካድሬ በአነጋገሩ ለተናደዱ የቀድሞ ወታደር ወገኖቻችን የሆነ ችግር ካላችሁ በመረዳዳት መፍታት እንችላለን ካለፉት የተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር በማያያዝ ሊያሳምናቸው የሞከረ ቢሆንም ተሰብሳቢዎች ግን ከአሁን በፊት መንግስት ያለምንም እገዛ አባሮን ሲያበቃ አሁን ምርጫ በተቃረበበት ሰዓት  ለጥቅሙ ሲል እኛን መጥራቱ ቅንነት አይደለም በማለት እንዳልተቀበሉት ለማወቅ ተችሏል።