Friday, February 13, 2015

በታች አርማጮና አብራጅራ የሚኖሩ የትግራይ ባለሃብቶችና ነጋዴዎች በአካባቢው ተወላጆች በንብረታቸውና በህይወታቸው ላይ ከባድ ጉዳት እንደወረደባቸው ለማወቅ ተችሏል።



ምንጮቻችን እንደገለፁት ስርዓቱ በሚለኩሰው ጥር 22/2007 ዓ.ም 3፣00 ሰዓት ጥዋት ላይ በአማራ ክልል በታች አርማጭሆና በአብረሃ ጀራ ለሚኖሩ ነጋዴዎችና ባለሃብቶች መሬታችንን ልቀቁልን በሚል ምክንያት በአካባቢው ተወላጆች በህይወታቸውና በንብረታቸው ላይ ግድያና ዘረፋ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ተገለፀ።
ከተገደሉትና ንብረታቸውን ከተዘረፉት ሰዎች የተወሰኑትን ለመጠቀስ ተስፋይ ባራኺ የተባለ የሃውዜን ተወላጅ የሆነ በቢላዋ ተወግቶ እንደተገደለና  የነበረው ቡቲክም የተዘረፈ ሲሆን እንዲሁም ተኸስተ ብርሃነ የተባለ የአድዋ ተወላጅ የነበረውን የኤልክትሮኒክስ ንብረት ከዘረፉት በኋላ ሰውየውንም በጥይት መተው እንደገደሉት ሊታወቅ ተችሏል።
በተጨማሪ ሓጎስ ብርሃነ ወዲ ሽረ። ገብረእግዚኣብሄር ወዲ ቀሺ የሰለኽለኻ ተወላጅ፤ ወ/ሮ ሚዛን ሓድጉና ሌሎችም በበትር የተደበደቡ ሲሆን በተለይ ወ/ሮ ሚዛን በደረሰባት ከባድ ድብደባ አካላዊ ጉዳት ደርሶባት እንደሚገኝ ሊታወቅ ተችሏል።
በህዝቡ መካከል ግጭት ተፈጥሮ የሰው ህይወት እየጠፋ እያለ የአካባቢው ፖሊሶች እጃቸውን አጣምረው ሁኔታውን እየተመለከቱት እንደሚገኙ የገለፀው ይህ መረጃ ይህ ደግሞ የኢህአዴግ ባለስልጣኖች ለህዝቡ በብሄር በጎሳ እያጋጩ ስልጣናቸውን ለማስቀጠል እያደረጉት ያለው ተንኮል መሆኑን ሁኔታውን እየተመለከቱ ያሉ አንዳንድ ወገኖቻችን በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።
ካጋጠምው እልቂት በኋላ የስርዓቱ አስመሳይ ካድሬዎችና የሁለቱ ካድሬዎች በዚህ ሰሞን ለማስመሰል ለሁለተኛ ጊዜ በአብደራፊ ከተማ ስብሰባ ለማድረግ ቀጠሮ የደረጉ እንኳ ቢሆኑም የክልል ሶስት የወረዳና የዞን አስተዳዳሪዎች  እዲሁም የፖሊስ አዛዦች አንመጣም በማለታቸው ግጭቱ እየቀጠለ ያለ ሲሆን ሁኔታውን ለማረጋጋት በማለት ከሁለቱ ክልሎች 800 ፌደራል ፖሊሶች በአብደራፊና አብረሃ ጅራ ፤በመተማ የ12 ክፈለ ሰራዊት በዳንሻና ጎንደር የ24 ክፈለሰራዊት ኩማንዶ ተሰማርተው እንደሚገኙ ሊታወቅ ተችሏል።