በአካባቢው የሚገኙ ምንጮቻችን እንደገለፁት በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን
ፀገዴ ወረዳ የሰሮቃ ከተማ ነዋሪዎች 60 ሚሊሻዎች የሚገኙባቸው ከ500 በላይ ዜጎቻችን የኢህአዴግን ብልሹ የመሬት አስተዳደር በመቃወም
ጥር 28 ቀን 2007 ዓ/ም ከሰዓት በኋላ ከ11 ሰዓት እስከ 1
ሰዓት ምሸት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳካሄዱ ሊታወቅ ተችሏል።
ይዘዋቸው ከተነሱት ዋነኛ ነጥቦች መካከል ለተነሳው የመሬት ግጭት በስርዓቱ
መፍትሄ እንዲያደርጉ ተብለው የተመለመሉት ሽማግሌዎች ቅንነት የላቸውም መንግስት አስታራቂ መስሎ በመካከላችን ገብቶ በህዝባችን ውስጥ
እያቀጣጠለው ያለው ህዝቡን የማነሳሳት ግጭት መቆም አለበት የሚሉና ሌሎችንም መፎክሮች በመያዝ እንደሆነ ከምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ ገልጿል።
ይህ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲካሄድ ካስተባበሩት ሰዎች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ
አሻግሬ ባንቴ የሚሊሻ ሃላፊ፤ ተስፋይ መንገሻ ሚሊሻና ኑርልኝ መኮነን የተባሉ የሚገኙባቸው እንደሆኑ መረጃው አክሎ አስታውቋል።