Sunday, April 12, 2015

በአማራ ክልል አዊ ዞን ዳንግላ ወረዳ አካባቢ የሚኖረው ህዝብ። ምርጫን አስመልክቶ ወደ በሚደረገው ስብሰባ እንዲወጣ የተደረገለትን ጥሪ መቃወሙ ተገለጸ፣



በአማራ ክልል አዊ ዞን ዳንግላ ወረዳ አካባቢ የሚኖረው ህዝባችን። በመጪው ግንቦት ወር ላይ የሚካሄደውን አስመሳይ ምርጫ አስመልክቶ። ስርአቱ ሊያካሂደው ወደ አሰበው ስብሰባ እንዲወጡ በማለት። መጋቢት 13/2007 ዓ/ም ያቀረበላቸውን ጥሪ እንደተቃወሙት የገለጸው መረጃው። በህዝቡ ተቃውሞ ስጋት ላይ የወደቁ የስርዓቱ ባለ ስልጣኖችም በንፁሃን ወገኖቻችን ላይ የማሰርና የማስፈራራት እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸውን የደርሰን መረጃ አስታውቋል፣
    ቀጣይ የሚካሄደውን አስመሳይ ምርጫ አሰመልክቶ በሚደረገው ስብሰባ ላይ አንካፈልም ብለው እስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ ከሚገኙት ብዛት ያላቸው ሰዎች መካከል። ስድስት የሚሆኑ ወገኖቻችን አነሳሾች ተብለው በመታሰራቸው። ህዝቡ ያለ አግባብ የታሰሩት ወገኖች ይፈቱ በማለት። የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄደ ባለበት በአሁኑ ሰዓት። የስርአቱ ፖለሶች በላያቸው ላይ ከባድ ግፍ እየፈጸሙ መሆናቸውን መረጃው አስረድቷል፣