Monday, April 6, 2015

በምዕራብ ጎጃም ዞን በሚገኙ ወረዳዎች ከፍተኛ የዘይት የስኳርና ሌሎችም አቅርቦቶች ችግር እያጋጠመ መሆኑን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረዱ፣




   እንደምንጮቻችን ዘገባ በዞኑ ከሚገኙ 15 ወረዳዎች የተወጣጡ  የግብርና ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊነት የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቅርንጫፍ በሆነው ቡሬ ካምፓስ አዳራሽና ትንሳኤ ሆቴል አዳራሽ እየተካሄደ ባለው ስብሰባ  በመምሪያ ሃላፊው አቶ ተስፋሁን መንግስቱ መድረክ መሪነት በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ለብዙ ጊዜ ሊቀረፍ ያልቻለው የዘይት የስኳርና ሌሎችም መንግስት ሊያቀርባቸው የሚገባቸው አቅርቦቶች ችግር በተደጋጋሚ በህዝብ እየቀረበ ምላሽ አያገኙም ማለታቸውን የገለፀው መረጃው አቶ ተስፋሁን መንግስቱ አጀንዳችን አይደለም በሚል ቢቃወምም ተሰብሳቢዎቹ በበኩላቸው ግን የወቅቱን የህዝቡን እሮሮና ችግር ጥለን በሌላ ጉዳይ ላይ ልንወያይ አንችልም በማለት መፍተሄ እስኪገኝ ድረስ ሊወያዩበት የወሰኑ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፣
   ይህ በዞኑ እየታየ ያለው አንገብጋቢ የዘይትና የስኳር አቅርቦት አለመኖር ከመጪው የፋሲካ በዓል ጋር ተያይዞ ለማህበረሰቡ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን ምንጮቻችን አስረድተዋል፣