Monday, April 6, 2015

በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ-ዳሞት ወረዳ የሚገኙ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች በስርዓቱ ተላላኪዎች እየተጨቆኑ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፣



በደጋ-ዳሞት  ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2007 ዓ/ም የመንግስትን ግፍና ጭቆናዎች ይፋ በማውጣት ለህዝባቸው እያስተማሩ  በተቃዋሚነት ይንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ወጣቶች ከስራ ገበታቸው እየተፈናቀሉ ቤት ንብረታቸውን መውረስና ዜጎችን ማሰር ማሰቃየት የተለመደ የመንግስት ባህሪ መሆኑን የገለፀው መረጃው።  በቅርቡም  መሰል አድማሴ የተባለ ወጣት ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ቤትህን አከራይተሃል በሚል ታስሮ ሲሰቃይ እንደቆየ አስረድቷል፣
   በተመሳሳይ የተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበረውና በባህርዳር ከፍተኛ መረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኘው የአቶ ጥላሁን አበበ ቤተሰቦችና ልጁ መምህር ተስፋየ ጥላሁን  በሚያስተምርበትና ቤተሰቦቹ በሚኖሩበት አካባቢ በተደጋጋሚ የመንግስት አሽከሮች እየተከታተሉ እየረበሿቸው መሆናቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል፣