Monday, June 29, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተካሄደው የይስሙላ ምርጫ ላይ አብዛኛው መራጭ ለተቃዋሚዎች መርጦ እያለ የኢህአዴግ ስርዓት አሸነፍን ማለቱ ከህዝቡና ከታዛቢው ወገን ተቃውሞ እያጋጠመው መሆኑን ከከተማው ተገለፀ።



በደረሰን መረጃ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ባለፈው ግንቦት 2007 ዓ/ም በገዢው የኢህአዴግ መንግስት አጭበርባሪነት እየተመራ በተካሄደው አስመሳይ ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ ህዝቡ ለተቃዋሚዎች ቢመርጥም የስርዓቱ ካድሬዎች ግን የህዝቡን ድምፅ በማጭበርበር ኢህአዴግ በተወሰነ አብላጫ ድምፅ እንዳሸነፈ አድርገው መግለፃቸው በህዝቡና በታዛቢዎች የተቃውሞ ሓሳብ መቅረቡን ታውቋል።
    በተለይ በጨርቆስ ክፍለ ከተማ በአራተኛና በአምስተኛ የምርጫ ጣብያ ውስጥ መራጩ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ተቃዋሚዎችን እንደመረጠ መሸፈን ያልቻሉትን የምርጫ ታዛቢዎቹ የስርዓቱ ባለስልጣናት አጭበርብረው አሸንፈናል ብለው በተናገሩበት ሰዓት የተፈፀመው ድርጊት አንቀበልም በማለት ከህዝቡ ጎን እንደቆሙ መረጃው ጨምሮ አስታውቋል።
    ከተፈፀመው የማጭበርበር ሁኔታ በመነሳት ሰኔ 15 ላይ ውጤቱ በሚነገርበት ሰዓት ህዝቡ ዓመፅ እንዳያስነሳ የሰጉት የስርዓቱ ባለስልጣናት በለገዳዲ አካባቢ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁት ሻምበሎችና እነሱን የሚያንቀሳቀሱ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች በተጠንቀቅ እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል።