Sunday, June 21, 2015

በትግራይ ክልል ዓብይ-ዓዲ ከተማ ሰረት ቀበሌ ውስጥ የሚኖር ህዝብ ሙሉ በሙሉ ዓረና/መድረክን እንደመረጠ ምንጮቻችን ከአካባቢው የላኩልን መረጃ ገለፀ።



    በመረጃው መሰረት በትግራይ ማእከላዊ ዞን ዓብይ-ዓዲ ከተማ  ሰረት ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ ሕብረተሰብ ህወሓትን በመቋወም ዓረና/መድረክ ሰለመረጠ የህዝቡ  ድምፅ ያልተዋጠላቸው የዞንና የወረዳ አስተዳዳሪዎች ህዝቡን ነጋ ጠባ በመሰብሰብ ለምን ህወሓት አልመረጣችሁም? ህወሓት እንድትጠሉ ያስገደዳችሁ ምክንያት ምንድነው? እያሉ ጫና በመፍጠር  ከእለታዊ ስራዎቹ እያደናቀፉት እንደሚገኙ ታውቋል።
   በነዚህ ባለስልጣናት ካድሬዎች በየቀኑ ሕወሓት ትታችሁ ለምን ዓረና መረጣችሁ በሚል ግምገማ የቀረበላቸው ነዋሪዎች ደግሞ” በችግራችን ጊዜ አይታችሁን  የማታውቁ አሁን ለዓረና/መድረክ ስለመረጥን ትመላለሳላችሁ፤ እኛ የመሰለንን መርጠናል፣” በማለት እንደመለሱሏቸው የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።