Sunday, June 21, 2015

በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ብር ቤቴ ላይ የተካሄደው የይስሙላ ምርጫ በስርአቱ ተላላኪዎች ስለ ተጭበርበረ ህዝቡ ምሬቱን በመግለፅ ላይ እንደሚገኝ ታወቀ።



    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በባህር ዳር ከተማ ብር ቤቴ በተባለው አካባቢ የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የህዝቡን ድምፅ በገዢው ስርአት ተላላኪዎች ተጭበረበረ በሚል ምክንያት ሁከትና ግርግር ሰለተነሳ በዚህ የተደናገጡት የስርአቱን ካድሬዎች ፖሊሶችና ምልሻዎችን በማሰማራት ህዝቡ እያስፈራሩትና ከቦታ ወደ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ እንደከለከሉት ለማወቅ ተችሏል።
   በተለይም ያቢ ጤና  በተባለው ወረዳ አካባቢ ተቃዋሚ ድርጅቶች እንዳይወዳደሩ በመከልከላቸው የተነሳ በርከት ያለ የምርጫ ካርድ የወሰደ ህዝብ ሳይመርጥ መቅረቱና ከዚህ በመነሳትም የስርአቱን ካድሬዎች ህዝቡን ሰብስበው ለምን እንዳልመረጠ በሚጠይቁበት ጊዜ “ ብንመርጥ ባንመርጥ ሁሉ በእጃችሁ ነው ሲል እንደመለሰላቸው መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።