Friday, June 12, 2015

መቐለ ከተማ ብዛት ባላቸው የፌደራልና የክልል ፖሊሶች መጨናነቋን ከቦታው ያገኘነው መረጃ ገለፀ።



   በኢህአዴግ የተካሄደውን የይስሙላ ምርጫ ተከትሎ የስርዓቱ ምርጫ ቦርድ በሁሉም የትግራይ ክልል ዞኖች ህወሃት/ኢህአዴግ አሸነፈ ብሎ መግለጫ ከሰጠ በኋላ በክልሉ የተወዳደሩት ፓርቲዎች በተለይም ዓረና/መድረክ የምርጫውን ውጤት ባለመቀበላቸው ምክንያት ህዝቡ ተቃውሞ እንዳያካሂድ ስጋት ላይ የወደቀው ገዢው ስርዓት የከተማዋን ፀጥታ ለመጠበቅ በሚል ሽፋን ከፌደራልና ከክልል የመጡ ፖሊሶች ቀንና ሌሊት እየዞሩ በነዋሪው ህዝብ ላይ ጫና እየፈጠሩ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከቦታው አስታቋል።
     መረጃው በመቀጠል ፖሊሶቹ ከቀበሌ 17፤ እንዳስላሴና እንዳ ጀወርጊስ በተባሉ አካባቢዎች በመነሳት ወደ መሃል ከተማ እንደተሰማሩና የመቐለን ከተማ ነዋሪዎች በተለይም ወጣቱን ማታ ላይ ስራውን ለማሳለጥና ለመዝናናት ብሎ ወደ ውጭ በሚወጣበት ጊዜ የማይረባ ጥያቄዎች በማቅረብ እያስጨነቁት መሆናቸውን የተገኘው መረጃ ጨምሮ ገልጿል።