Friday, June 12, 2015

የኢህአዴግ ስርዓት በደቡብ ህዝቦች ክልል ውስጥ ራሱ እየፈጠረው ባለው ግጭት ምክንያት ንፁሃን ወገኖች እየታደኑ በመታሰር ላይ መሆናቸው ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።



   በመረጃው መሰረት በደቡብ ህዝቦች ክልል፤ ደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ፤ ኦሞ-ሃና ቀበሌ በተባለው አካባቢ የስርዓቱ ካድሬዎች በሁለት ጎሳ መካከል ባስነሱት ግጭት ምክንያት ከሁለቱም ወገን የሞቱና የቆሰሉ መኖራቸውን የገለጸው መረጃው ይህንን ምክንያት በማድረግም ፌደራል ፖሊስና የክልሉ ፖሊሶች በጋራ በመሆን የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት የፈጠሩት ተንኮል ነው በማለት ግንቦት 26 /2007 ዓ/ም አምባቸው ታየ አድነው የተባለ የመድረክ አባል የሚገኝባቸው 10 ሰዎችን ጠልፈው ወደ ሃዋሳ ከተማ እንደወስዷቸው ለማወቅ ተችሏል።
   መረጃው በማስከተልም ይህ በተደጋጋሚ እየተካሄደ ያለው የጎሳ ግጭት ሆን ተብሎ ስርዓቱ ህብረተሰቡን ለማለያየትና አድነት እንዳይኖረው የሚፈፅመው ተንኮል እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድቷል።