Sunday, June 21, 2015

በአማራ ክልል ዳንግላ ከተማ ውስጥ የተካሄደው የይስሙላ ምርጫ ህዝቡ ቅንነት የጎደለው ነው በማለት አንመርጥም ስላለ በርከት ያሉት ዜጎቻችን እየታሰሩ እንደሚገኙ ተገለፀ።



የተገኘው መረጃ እንዳስረዳው የዳንግላ ከተማ ነዋሪ ህዝብ በ2007ዓ/ም የይስሙላ ምርጫ ላይ አንሳተፍም በማለት ያልመረጠ ሲሆን አንመረጥም በማለታቸው የተነሳ በገዢው ጉጅሌ ስርአት ከታሰሩት ዜጎች ለመጥቀስ ያክል ተስፋየ አባተ፤ በለጠ ገረመው፤ ባህሩ ካሳ፤ ሽዋየ ብሩና አደሬ መኮነን የተባሉት ንፁሃን ዜጎች እንደሚገኙባቸው ታውቋል።
   የነዚህ ዜጎች የታሰሩበትን ምክያት ደግሞ ለምን ምርጫ አልመረጣቹሁም? ምን የተማመናችሁበት ነገር አለ? የሚል እንደሆነ የገለጸው መረጃው እየተወሰደ ባለው ህጋዊነት የሌለው የማሰርና የማስፈራራት እርምጃም ነዋሪው ህዝብ ከተወለድንባት ሃገራችን ወዴት እንድንጠፋ ፈለጉን፤ ብንመርጥ ባንመርጥ  መብታችን ነው ለምንድነው የምንታሰረው በማለት ምሬቱን በማሰማት ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።