በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ማእከላዊ ዞን አሕፈሮም ወረዳ ነዋሪ
የሆኑት የዓረና መድረክ አባላት ገዢው ስርአት በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ አሸነፍኩኝ እያለ ባለበት ጊዜ ተቃዋሚዎች ደግሞ ውጤቱን
አንቀበልም በማለታቸው የተነሳ አመፅ ለማንሳት ሰዎች አድራጅታችሁ በመንቀሳቀስ ላይ ናችሁ በሚል የሃሰት ውንጀላ ግንቦት
26/2007 ዓ/ም ታስረው ወደ መቐለ ከተማ እንደተወሰዱ ለማወቅ ተችሏል።
ሰላማዊውን ትግል አምነው ሲንቀሳቀሱ ጠንካራዎች የነበሩት ሰዎች በሚያደረጉት
ክርክር ብቻ ባልዋሉበት የሃሰት ወንጀል ተከሰው ወደ ዘብጥያ ከተወረወሩት ወገኖች መካከል ክንፈ ወልደ ሚካኤልና ንጉሰ ኪዳነማሪያም
የተባሉት ዜጎች ከእንትጮ ከተማ ታስረው እንደተወሰዱ ምንጮቻችን ገልጸዋል።