Friday, July 24, 2015

በአዲ ሃገራይ አካባቢ የሚገኝ ለግዜው ስሙ ያልታወቀው ወታደር 3ት ኮነሬሎችና ሌሎች በርከት ያሉት ወታደሮች በመግደል ራሱን እንዳጠፋ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ገለጸ።



      ከሰሜን የደረሰን መረጃ እንዳስረዳው በገዢው የኢህአዴግ ስርአት መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ታስረው የሚገኙ ወታደሮች የሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች በሚከተሉት ከፋፋይ አሰራር ምክንያት ተማርረው የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ መሆናቸውን የገለጸው መረጃው አሁንም በአዲ ሃገራይ አንድ ወታደር ለ3 ኮነሬሎች ከነ አጃቢዎቻቸው በኡርምታ ቶክስ በመግደል ለራሱም ህይወቱን እንዳጠፋ ለማወቅ ተችሏል።
    ይህ በያዝነው ሳምንት በ3 የኢህአዴግ ኮነሬሎች ላይ የተውሰደው እርምጃ ለብዙዎቹ በላያቸው ልይ ግፍ ሲፈፀምባቸው የነበሩ ወታደሮች እርካታ የሰጠ መሆኑና ሌሎች አዛዦችም በላያቸው ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እንዳይወሰድባቸው ስጋት መግባታቸውን የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።