Friday, July 24, 2015

በዓዲ-ግራት ከተማ የሚገኘው ህዝብ ከመጠን በላይ ግብር እንዲከፍል በስርዓቱ እየተገደደ መሆኑ ታወቀ።



    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በዓዲግራት ከተማ የሚኖር ህዝብ በህወሃት ኢህአዴግ ካድሬዎች ከአቅም በላይ ግብር እንዲፍል እየተገደደ መሆኑን የገለፀው መረጃው ከመጠን በላይ ግብር እንዲከፍሉ እየተገደዱ ካሉትም አቶ ኪሮስ ካሕሳይ የአጋሜ ሆቴል ባለቤት 285 ሺ ብር፤ አቶ ሃይሉ ወልደማርያም የቤት አካራይ 75 ሺ ብር፤ አቶ ብርሃነ ሕሸ የልብስ መሸጫ መደብር ባለቤት 120 ሺ ብር፤ መምህር ዘርኢት የቤት አካራይ 120 ሺ ብር በግድ ክፈሉ መባላቸውና ባጠቃላይ ህዝቡም በተፈጠረው ሁኔታ ብሶቱ ቢገልፅም ሰሚ አካል እንዳላገኘ መረጃው አታውቋል።
    እነዚህ ከላይ የተገለፁትን ተጠቂዎች ለማሳያ የቀረቡ እንጂ በመላው ያገራችን አካባቢዎች በርካታ ህዝብ ከገቢው ጋር የማይመጣጠን ግብር ክፈል እየተባለ በስርዓቱ ካድሬዎች እየተገደደ መሆኑና በህዝቡ የሚቀርቡት አቤቱታም ሰሚ ጀሮ እንዳላገኙ የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።