Thursday, July 30, 2015

በባህር ዳር ከተማ በከባድ ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩት ሰዎች ለፖሊስ አዛዦች ጉቦ እየሰጡ ከእስር በመውጣት ላይ መሆናቸው የደረሰን መረጃ አስረድቷል።



በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ሃምሌ 7 /2007ዓ/ም ሁለት ሰው ገድለሃል ተብሎ በጥርጣሬ የታሰረው መዃንንት ይርሳው የተባለ ግለሰብ ከእስርቭ እንዲለቀቅ በማለት ለኢንስፔክተር ብርሃኑ በላቸው ለተባለ የፖሊስ አባል 40ሺ ብር ጉቦ ስለሰጠው ኢንስፔክተሩም በሌሊት ፈትቶ እንደለቀቀው ምንጮቻችን ከላኩት መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
   ምንጮቻችን ጨምረው እንደገለፁት የፖሊስ አዛዡ አስቀድሞ ገንዘብ ስጠኝ እንጂ በሌሊት ሸሽተህ እንደሄድክ አስመስየ እለቃህአሎህ እንዳለው የሰሙ ሰዎች ለሚመለከታቸው አካላት ቢያስታውቁም ኢንስፔክተሩ ግን እስከ አሁን ድረስ የሚጠይቀው የመንግስት አካል እንዳላገኘ መረጃው ጨምሮ አስረዷል።