Thursday, July 30, 2015

በዓድዋ ከተማ ለስፖርት ተብሎ የተመደበውን በጀት ስራ ላይ ሳይውል በባለስልጣኖቹ ስለተጠፋፋ የተቃውሞ ሰልፍ መካሄዱን ተገለፀ።



    በትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ በዓድዋ ከተማ ውስጥ ለሚካሄዱ ለተለያዩ የስፖርት ማንቀሳቀሻ እንዲውል ተብሎ የተመደበውን ገንዘብ ባለስልጣኖቹ እንዳጠፋፉት ያወቁት አንድ ሺ ሦስት መቶ(1300) የከተማዋ ስፖርተኞች ባለፈው ሳምንት ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸውን የገለፀው መረጃው ከክልል የመጡትን ባለስልጣናት ሰልፉን ለማረጋጋት ቢሞኩሩም እናንተስ ከነሱ ምን የሚለያችሁ ነገር አለ በማለት ሃሳባቸው እንዳልተቀበሉት ለማወቅ ተችሏል።
    የተቃውመው ሰልፉን ለማረጋጋት ወደ ከተማዋ ከገቡ ባለስልጣናት ውስጥ አንዱ የሆነው የትግራይ ክልል ማሕበራዊ ጉዳይ ሓላፊ አለም ገብረዋህድ ተቃውሞውን ለማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ እያደረገ በነበረበት ሰዓት ሰልፍኞቹ በቦኩላቸው ይዟት የነበረውን መኪና በርዋና መስተዋትዋን ሰብረው ሲያበቁ በውስጥዋ የነበረው ወንበርም አውጥተው መጣላቸውን የተገኘው መረጃ ያስረዳል።