Thursday, July 30, 2015

የሁመራ ከተማ ነጋዴዎች መጠኑን ያለፈ ግብር ክፈሉ እየተባሉ በመገደድ ላይ በመሆናቸው የተነሳ በስርአቱ ላይ ምሬታቸው በማሰማት ላይ እንዳሉ ተገለፀ።



በትግራይ ምእራባዊ ዞን ሁመራ ከተማ የሚኖሩ ባለ ሃብቶች ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ግብር ክፈሉ ተብለው እየተገደዱ እንዳሉ የገለፀው መረጃው በውጤቱም ህዝቡ ተቃውሞ በማሰማት ላይ በመሆኑ የከተማው ካድሬዎች በከባድ ስጋት ላይ መውደቃቸው ታወቀ።
     በሁመራ ከተማ ነዋሪዎች ተነስቶ ያለውን ግርግር ለመግታት ታስቦ የከተማው ከንቲባ  አለሙ በየነ  የተባለው ካድሬ ሃምሌ 12 /2007 ዓ/ም ባለ ሃብቶች በመሰብሰብ ትክክለኛ ያልሆነውን የግብር አከፋፈል እናስተካክለዋለን በማለት ህዝቡን ሊያታልል የሞከረ ቢሆንም ተሰብሳቢዎቹ በዚህ ሃሳብ አንታለልም በማለት ተቃውሟቸውን እየቀጠሉ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።