Tuesday, August 11, 2015

በምእራብና በሰሜን እዝ ከሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ለምስራቅ እዝ ተጨማሪ ሃይል እንዲሆኑ በማለት ሃምሌ 19/2007 ዓ/ም ወደ ሱማሌ ክልል ተመልምለው መሄዳቸው ታወቀ።



በደረሰን መረጃ መሰረት ምስራቅ እዝ የሚገኘውን ሰራዊት ወደ ሶማሌ እንዲሄድና መስዋእትነት እንዲከፍል መደረጉን የገለጸው መረጃው አሁንም ተጨማሪ ከምእራብና ከሰሜን እዝ ሓምሌ 19/ 2007 ዓ/ም ወደ ጎረቤት አገር ሶማሊያ  እንዲሄዱ መደረጉን ተገለጸ።
    የስርዓቱ ባለስልጣናት የሃገሪቱ ሉአላዊነት ሳይነካ ምእራባዊያን ሃገራት የሚሰጡትን ትእዛዝ ተቀብለው ያገሪቱን ሰራዊት በገንዘብና በመሳሪያ በመሸጥ ላይ መሆናቸውን የተለያዩ ህብረተሰብ አካላት ምሬታቸውን እየገለፁ መሆናቸው ለማወቅ ተችሏል።