Tuesday, August 11, 2015

በአማራ ክልል ደሴ ከተማ ውስጥ ሁለትና ከዚያ በላይ ሆነው የሚንቀሳቀሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፖሊስ ተይዘው እየታሰሩ መሆናቸው ታወቀ።



    በደሴ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሁለትና ከዛ በላይ ሆነው የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች በክልሉ ፖሊሶች ኢ-ሰብአዊ በሆነ መንገድ እየተደበደቡና እየታሰሩ መሆናቸውን የገለጸው መረጃው ታስረው እየተሰቃዩ ከሚገኙት መካከልም ደሴ ከተማ 03 ቀበሌ  የሚኖረው ታከለ መንግስቴ፤ በተመሳሳይ ነዋሪነቱ ደሴ ከተማ 02 ቀበሌ የሆነው መክይ አብዶና በተለምዶ አጠራር አሬራ ተብሎ በሚጠራ ሰፈር ውስጥ የሚኖር ሉባባ ሁሴን እንደሆኑ የደረሰን መረጃ ገለፀ።
    በአሁኑ ወቅት የኢህአዴግ ካድሬዎች፤ የነሱን ተላላኪ የሆኑት የደህንነት አካላትና የፖሊስ አባላት አንድ ላይ በመሆን ህዝቡ በጋራ ተንቀሳቅሶና አብሮ እንዳይኖር የመለያየት ስራ እየሰሩ መሆናቸው የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።