Tuesday, August 11, 2015

የዓዲግራት ከተማ ነጋዴዎች ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠንና ከዓቅማቸው በላይ በሆነ መንገድ ግብር እንዲከፍሉ በመገደዳቸው ምክንያት ድርጅታቸው ለመዝጋት እንደተገደዱ ከከተማው የደረሰን መረጃ ገለፀ።



    በመረጃው መሰረት በተግራይ ምስራቃዊ ዞን በዓዲ ግራት ከተማ ውስጥ የሚገኙት በንግድ ስራ ላይ የሚተዳደሩ ወገኖቻችን ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ግብር እንዲከፍሉ መገደዳቸውና ፍትሃዊ ያልሆነ ግብር እንዲከፍሉ ከታዘዙት መካከልም አቶ ገብረዮውሃንስ ሃይሉ የኮምፒዩተር ጥገና ድርጅት ባለቤት 1,5 ሚልዮን ብር፤ ወ/ሮ አበባ የቤት አካራይ 13 ሺ ብር እንዲከፍሉ ከተደረጉ ጥቂቶቹ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃው በማከል የስርዓቱ ባለ ስልጣናት በግብር አተማመን ላይ ከፖለቲካዊ አመለካከት ጋር በማያያዝ የወሰኑት በመሆናቸው ምክንያት ነዋሪዎቹ በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ቅሬታ በምሬት እየገለፁ መሆናቸው የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።