Tuesday, August 11, 2015

አብደ ራፊዕ አካባቢ በአማራና በትግራይ ክልል ነዋሪዎች የተፈጠረው ግጭት ለበርካታ ወገኖች መሞት ምክንያት እየሆነ እንደሚገኝ ከአካባቢው ያገኘነውን መረጃ አስታወቀ።



    በመረጃው መሰረት በአብደራፊዕ አካባቢ በትግራይና በአማራ ነዋሪዎች ላይ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ከሁለቱም ክልሎች በርካታ ሰው መሞቱና መፈናቀሉ የገለጸው መረጃው  በአካባቢው ከትግራይ ክልል ኢንቨስት ሲያደርጉ የቆዩት ዜጎች በተከሰተው ሁኔታ ሰግተው ህይወታቸውን ለማዳን ሲሉ የጀመሩትን ስራ ለመተው መገደዳቸውና ለከፍተኛ ኪሳራ መጋለጣቸው ተገለፀ።
    መረጃው ጨምሮ ስራ ጅምረው ካቋረጡት ኢንቨስተሮች ለመጥቀስ ያህል አደራጀው ሓጎስ የተባለ የዓድዋ ተወላጅ የነበሩትን 3 ትራክተር ይዞ ከአካባቢው መውጣቱና በሁለቱም ክልሎች መካከል ተፈጥሮ ያለው ያለመረጋጋትም በስርዓቱ ምንም ዓይነት እርምጃ ባለመወሰዱ ምክኒያት ሁኔታው ወደ ከፋ ግጭት እያመራ መሆኑንና የአካባቢው ነዋሪዎቹም ስጋታቸውን እየገለፁ እንደሆኑ መረጃው አክሎ አስረድቷል።