Tuesday, August 11, 2015

በባህርዳር ከተማ ውስጥ ሁለት የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በፈንጅ መጋየታቸው ተገለጸ።



     በተገኘው መረጃ መሰረት በአዲስ አበባ ባህርዳር መስመር ተመድበው እየሰሩ የቆዩትን ሁለት ’‘ሰላም” በመባል የሚታወቁ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ከአዲስ አበባ ተነስተው ባህርዳር መናሃሪያ ከደረሱ በኋላ ሓምሌ 20/2007 ዓ/ም ከለሊቱ 6፣00 ሰዓት ላይ ሁለቱም መጋየታቸው ታወቀ።
    እነዚህ በፈንጅ ከስራ ውጭ የሆኑ አውቶብሶች ከአዲስ አበባ ባህርዳር የሚሰሩ ሆነው ፈንድቶ ያቃጠላቸውን ፈንጅ በማን እንደተጠመደ የታወቀ ነገር እንደሌለ፤ አውቶብሶቹ ከመቃጠላቸው ባለፈም በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት መኖሩን እስካሁን ድረስ የተገኘ መረጃ እንደሌለና ይህ ሁኔታም በህዝቡና በሹፌሮች ላይ ስጋት መፍጠሩን ከአካባቢው የተገኘው መረጃ አስታውቋል።