Monday, August 31, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊሶች ለመቅጠር ማስታወቂያ ቢያወጡም ለመቀጠር የሚፈልግ ሰው እንዳልተገኘ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



    በደረሰን መረጃ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከመጋቢት ወር ጀምረው በተከታታይ ለሦስት ወር ያህል ማስታወቂያ ቢወጣም ለመግባት ፈቃደኛ የሆነ ሰው ስለጠፋ ወደ ክልሎች ማስታወቂያው እንዲወጣ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።
    በአገራችን ውስጥ በኢህአዴግ አመራሮች ስጋት ምክንያት ነባር ፖሊሶችን ከጠላት ጋር ግንኙነት አላችሁ እየተባሉና የያዙት ሞባይል በየቀኑ እየተፈተሸ በርካታ ወጣቶች በመታሰራቸው ምክንያት አዲስ ፖሊሶች ለመቅጠር የወጣውን ማስታወቂያው ህዝቡ እንዳልተቀበለው መረጃው አክሎ አስረድቷል።