Monday, August 31, 2015

በአፋር ክልል የሚገኘው ነዋሪ ህዝብ፣ ነሃሴ 12/2007 ዓ/ም የክልሉ መንግስት በመቃወም በአዋሽ አርባና አዋሽ ስባት ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ፣፣



     በደረሰን መረጃ መሰረት የአፋር ክልል ህዝብ ነሃሴ 11/2007 ዓ/ም በአዋሽ አርባና አዋሽ ሰባት በተባሉ ከተሞች ውስጥ እኛን እያስተዳደሩ ያሉት የአማራና የትግራይ ተወላጆች ናቸው፤ እኛ በክልል መጠራታችን ምን ያደርግልናል ብለው ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውና የክልሉ መንግስት ፖሊሶች በማሰማራት እንዲደበደቡና እንዲበተኑ ማድረጉን ታውቋል።
    ህዝቡ በወቅቱ ለክልሉ መንግስት ያቀረበው ጥያቄ የአፋርን ህዝብ እየመሩት ያሉት ከሰሜን ወሎ፤ ከደቡብ ወሎና ከትግራይ የመጡ እንጂ የአካባቢው ተወላጆች አይደሉም፤ መሬታችንም ከአማራ ክልል በመጡ እየተጠቀሙበት ነው በማለት ብሶታቸው እየገለፁ እንደሆኑ መረጃው አክሎ አስረድቷል።