Wednesday, August 12, 2015

በትግራይ ክልል ስሜናዊ ምእራብ ዞን ልዩ ቦታ በርቀ ላፅያ በተባለው ድንበር አካባቢ የሚገኙ አርብቶ አደሮች በስርዓቱ የመከላከያ ቃኝ ወታደሮች እየተደበደቡና እየታሰሩ መሆናቸው ታወቀ።



     በደረሰን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል ስሜናዊ ምእራብ ዞን የሚገኙ አርብቶ አደሮች ሃምሌ 11/ 2007 ዓ/ም ላይ ብርቀላፅያ በተባለው ድንበር አካባቢ ጉዑሽ መብራህቱ የተባለውን ግለሰብ ከትህዴን ጋር ግንኝነት አለህ በሚል ከሃቅ የራቀ እውነታ የመከላከያ የስለያ ምድብተኞች ከህግ ውጭ በሆነ መንገድ ደብድበው ከብቶቹን በረሃ ላይ ጥለው ግለሰቡን ሽሬ ወታደራዊ እስር ቤት ወስደው ማሰራቸው ለማወቅ ተችሏል።
    የስርዓቱ የመከላከያ ሰራዊት የትግራይን ህዝብ ከትህዴን ጋር ግንኝነት አለህ በሚል የሃሰት ውንጀላ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ኑሮውን የሚመራ የአካባቢውን ነዋሪ እያሰቃዩት መሆናቸው የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።