Wednesday, August 12, 2015

በማእከላዊ እዝ ውስጥ ሓምሌ 27/2007 ከሬጅመንት አዛዥ እስከ እዝ አመራሮች ያቀፈ ስብሰባ መካሄዱ ከእዙ የውስጥ አዋቂዎች አፈትልኮ የተገኘ መረጃ አመለከተ።



    በመረጃው መሰረት በማእከላዊ እዝ ከሬጅመንት አዛዥ እስከ እዝ አመራር የተሳተፉበት ግምገማ ያለ ውጤት መጠናቀቁና ስብሰባውን ረግጠው ከወጡትም የ8ኛ ሬጅመንት ድጋፍ ሰጪ ሜካናይዝድ ም/አዛዥ ሻለቃ አደራጀው ሓጎስ እንደሆነ የገለፀው መረጃው መድረኩ ላይ የቀረበውን በትግራይ ተወላጆች ላይ ምንም ዓይነት በደል አልደረሰም የሚል ማጠቃለያ ሃሳብ በመቃወምና መድረኩን ይመራ ከነበረው አመራር ጋር በነበረው ያለመግባባት ምክንያት ስብሰባውን ረግጦ መውጣቱን ታውቋል።
    በወቅቱ የነበረው የመወያያ ርእስ አገራችን በመገንባት ችግሮቻችን እናስተካክል የሚል እንደነበረና አብዛኛው የስብሰባ ተካፋይም እንዳልተቀበለው መረጃው አክሎ አስረድቷል።