Friday, November 27, 2015

የወለጋ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች አብዛኛው ጊዜ የገዢው ኢህአዴግ የፖለቲካ ትምህርት እንዲማሩ እየተገደዱ ባሉበት ተቃውሞ ያሰሙት ተማሪዎች ተጠልፈው በመጥፋት ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ።



በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ ወለጋ ዩንቨርስቲ ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች አብዛኛው ጊዜ ትምህርታቸው በገዢው የኢህአዴግ ፖለቲካዊ ትምህርት እንደሚያሳልፉት የገለፀው መረጃው የስርአቱ ፖለቲካዊ ትምህርት የተቃወሙት በርከት ያሉት ተማሪዎች ደግሞ ፀረ ልማታዊ መንግስታችን ናችሁ እየተባሉ በፀጥታ አባላት ታፍነው እየተወሰዱ አድራሻቸው በመጥፋት ላይ እንደሚገኙ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አስገነዘበ።
       የኢህአዴግ የፖለቲካ ትምህርት በመቃወም ተፍነው ከተወሰዱት ተማሪዎችም ታረቀ የተባለ የ5ኛ አመት ኢንጅነሪግ ተማሪ ኣንድ ሲሆን የትምህርት ጓደኞቹ የሆኑት ተማሪዎች ደግሞ ስለ ሁኔታው ለማወቅ ወደ ዩንቨርስቲውና የከተማ አስተዳደር በመሄድ በሚጠዩቁበት ጊዜ ለጊዜው አስረን እንፈታዋለን በሚል አስመሳይ መልስ ቢስጧዋቸው እንኳ እስከ አሁን  ድረስ የተማሪው አድራሻ እንዳልታወቀ ምንጮቻችን ጨምረው ገልፆዋል።