Friday, November 27, 2015

በመቱ ዩኒቨርስቲ ከሚማሩ ተማሪዎች የኢህኣዴግ ባለ ስልጣናት ባሳማፘቸው ታጣቂዎች ተገድለው እየተጣሉ እንደሚገኙ ተገለፀ።



   በኦሮምያ ክልል መቱ ዩንቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች ለፀረ ህዝብ የወያኔ ኢህኣዴግ ስርአት አሰተዳደር በመቃወም የተለያዩ ጥያቄዎች እያነሱ ለባለ ስልጣናቱ እያስጨነቁዋቸው እንደሚገኙ የገለፀዉ መረጃው ይሄንን ለመሰለ ተቃዉሞ ያነሳሳሉ ተብለው ለተጠረጠሩ ተማሪዎች በለሊት በመዉሰድ እንዲገደሉ እያደረጉ መሆናቸው በቦታዉ የሚገኙ ምንጮቻችን ከላኩት መረጃ ለማወቅ ተችለዋል።
  ታጣቂዎቹ መጥፎ ተግባራቸው በመቀጠል ቴሬሳ ሰሬሳ ለተባለ የዩንቨርስቲው ተማሪ የተቃዋሚ ድርጅቶች ደጋፊ እና ተባባሪ ስለ ሆነ ተማሪዎች እያነሳሳ ነው በማለት እየፈለጉት ከቆዩ በኃላ በጥቅምት 20 2008 ዓ.ም በለሊት ተገድሎ ተጥሎ  በመገኘቱ የዩንቨርስቲው ማህበረሰብ በስርኣቱ ፖሊሶች እና ታጣቂዎች ነው የተገደለው እያሉ እንደሚገኙ ተገለፀ።