Tuesday, December 1, 2015

በደባት ከተማ የሚኖር ህብረተሰብ ለ35ኛ ኣመት ምስረታ ብአዴን ድርጅት በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ ለመዉጣት ፍቃደኛ እንዳልሆነ ተገለፀ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በኣማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ደባት ከተማ የሚኖር መላው ህብረተሰብ ጥቅምት 28/2008 ዓ.ም ለ35 ኣመት የበኣዴን ድርጅት ምስረታ በኣል ድጋፍ የሚያሰማበት ስላማዊ ሰልፍ እንድያካሂድ በድርጅቱ ካድሬዎች ለቀረበለት ጥሪ በመንፈግ የሆነ ይሁን ለበኣሉ የሚመልከት ዝግጅት እንደማያደርግ በመግለፅ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችለዋል።
    መረጃው ጨመሮ እንዳስረዳው በከተማው የሚኖር ህዝብ ባለፉ 24 ኣመታት የብኣዴን ኢህአዴግ የስልጣን ዕድሜ ለተቃዋሚ ድርጅቶች ትደግፋለህ እየተባለ ሊሰሩ የሚገባቸው የመሰረተ ልማት ስራዎችና ማህበራዊ ኣገልግሎቶች ለማግኘት ባለ መቻሉ በገዢው ስርኣት ላይ ተደጋጋሚ ተቃዉሞዎች እያካሄደ እንደቆየ ታዉቀዋል።