Tuesday, December 1, 2015

የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች ባጋጠመ ከባድ ድርቅ ምክንያት ለከባድ ማህበራዊ ችግር ተጋልጦ በሚገኝበት ወቅት የሚደርስለት የመንግስት አካል እንዳላገኘ ለማወቅ ተችለዋል።



በኣማራ ክልል ስሜን ወሎ ዞን ሶቆጣ ከተማ የሚኖር መላው ህብረተሰብ በድርቅ ምክንያት ለከባድ ረሃብ ተጋልጦ እንደሚገኝ የጠቆሞው መረጃው ይህ ግዜ የማይሰጥ የምግብ እጥረት በከተማው ኣጋጥሞ እንዳለ የሚያዉቁ የስርኣቱ ባለ ስልጣናት  ለህዝቡ ትኩረት ስጥተው ሊደረግ የሚገባዉ ደገፍ ሊያድርጉ ባለመቻላቸው ነዋሪዎቹ ኣገራቸው እየለቀቁ በመሰደድ ላይ መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል።
      መረጃው በማስከተል ወደ ኣከባቢው የሚገባ ብቁ ኣገልግሎት የሚሰጥ ፅርግያ ካለ መኖሩ በእግራቸው የሚጋዙ ዜጎች ረሃብ እና ጥማት ተጨምሮበት ለተለያዩ በሽታ እና ሌሎች ችግሮች እየተጋለጡ እንደሚገኙ ከብቶቻቸው ቢሆኑም ከሰው በከፋ መልኩ ብረሃብ ተሰቃይተው እየመቱ እንደሚገኙ በኣካባቢው የሚገኙ ምንጮቻችን ጨምረው ኣስረድተዋል።