Sunday, December 6, 2015

በአሁኑ ግዜ በትክል ድንጋይ ወረዳ የምትተዳደርው ሮቢት የምትባለው ስፍራ በተደጋጋሚ ግጭት እየተካሄደባት መሆኑን ምንጮቻችን ከስፍራው አስረድቷል ።



     በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአሁኑ ግዜ በትክል ድንጋይ ወረዳ የምትተዳደርው ሮቢት የምትባለው ስፍራ በተደጋጋሚ  ግጭት እየተካሄደባት መሆኑንና  ከዚህ በፊት በስፍራው በፈደራል ፖሊስና በቤተ እስራእላውያን መካከል ግጭት ያጋጠመ ሲሆን ኣሁንም ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ግጭት ተፈጥሮ እንዳለ ታውቀ።
              በዚህም መስረት ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ለተነሳው ግጭት ለእርዳታ ተብለው ከ24 ክፍለ ጦር  ከ70 እስከ 80 የሚሆኑ ወታደሮች  በህዳር 1/ 2008 ዓ/ም  በመኪና  ተጭነው ከሳንጃ ተነስተው ግጭቱ  ወደ  ተነሳበት ሮቢት በተባለው ስፍራ ለመደረስ በሚጓዙበት ግዜ  ነዋሪው ሕብረተሰብ ኣስቀድሞ ስለ ነቃበት በመንገዱ ላይ መሰናክል በመፍጠር መኪናዋን እንድትገለበጥ ሰለ አደርጉ በዚህም ሳቢያ 40 ወታደሮች ሲሞቱ የቀሩት በከባድ ቆስለው በባህርዳርና በኣዘዞ  በሚገኘው ሆስፒታል ገብተው በመታከም ላይ መሆናቸወን ታወቀ።
         መረጃው ጨምሮ በዚሁ በተፈጠረው ግጭት ከ25 በላይ የሮቢት ነዋሪዎች በመከላከያ ሰራዊት መገደላቸውና በዚህ ምክንያትም በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት ሰለ ተፈጠረ በኣከባቢው የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞችም ህዝቡ አታስፈልጉንም ብሎ ሰለ ኣባረራቸው ገዥው ሰርአቱም በበኩሉ ነዋሪው ህዝብ ሲገለገልበት የነበረውን የህክምና ጣብያዎችና ትምህርት ቤቶችን እንዲዘጉ ማድረጉንና ለዚህ ግጭት ያነሳሱ ሰዎችም ሆን ብለው የአባይን ግድብ ለማደናቀፍ በግብፅ መንግስት የታጠቁ ናቸው በሚል ምክንያት  በሕብረተሰቡ ላይ የተለያዩ  ከፍተኛ ግፍ  በመፈፀም  ላይ መሆኑን  ለማወቅ ተችሏል።